Telegram Group Search
⬆️
ሁለት አሳዛኝ ክስተቶች!

የመጀመርያው ክስተት ያጋጠመው ባለፈው ቅዳሜ ፒያሳ አካባቢ ሲሆን ከካናዳ ለበአል የመጣ እና ሚካኤል ገብሩ የተባለ ግለሰብ በዘረፋ መሀል ባጋጠመው ድብደባ ህይወቱ አልፏል። ስለወንጀሉ ዝርዝር መረጃ ከአ/አ ፖሊስ ጠይቄ እስካሁን መልስ አላገኘሁም። ሚካኤል ባለፈው አመት ካናዳ ውስጥ የ10 ሚልዮን ዶላር ሎተሪ አሸንፎ እንደነበር ከሚያውቁት ሰዎች መረጃ ደርሶኛል።

ሁለተኛው ክስተት ደግሞ ባለፈው ማክሰኞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኛ የሆነች እፀገነት የተባለች ግለሰብ ቱሉ ዲምቱ አካባቢ ህይወቷ አልፎ መንገድ ዳር ተገኝታለች። አንድ የቤተሰብ አባል እንደነገረኝ እፅገነት ለስራ በጠዋት ወጥታ በባጃጅ ወደ ሰርቪስ መኪና ስትሄድ መኪናው ጋር ሳትደርስ ኮብልስቶን ዳር ተገኝታለች። እስካሁን አሟሟቷ ምን እንደሆነ እንዳልታወቀ እና አንድ ሰው ግን "በመታነቅ" ህይወቷ ሳያልፍ እንዳልቀረ እንደነገረው ገልፆልኛል። ጨምሮም "የተፈጥሮ ህልፈት ነው እንዳይባል ምንም ህመም የለባትም። ጠቅላላ የህክምና ውጤቱን ግን ከሆስፒታል ጠይቁ ተብለናል። ብቻ ያው እኛ ትናንት ቀብረናታል" ብሏል።

ነብስ ይማር! @ethio27
የአገው ብሔራዊ ሸንጎ በሰቆጣ ከተማ ውይይት አድርጓል።
https://www.facebook.com/100006093696199/posts/2467628626783570/
ንግድ ባንክ የሰራተኞቹን ደመውዝ በእጥፍ አሳደገ!!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ በሐምሌ 2011 ባካሄደው ስብሰባ የባንኩ ሰራተኞች ለሁለት አመታት ሲያቀርቡ የነበሩትን የደመውዝ ጭማሪ ጥያቄ ተቀብሎ ከያዝነው የበጀት አመት ጀምሮ የሚታሰብ የ100% ጭማሪ እንዲደረግ አፅድቋል። የጭማሪው መጠን ሰሞኑን በውስጥ ማስታወሻ ይታወቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ: አዲስ ማለዳ
@ethio27
"የኢትዮጵያ የብልፅግና ፓርቲ" በሚል ስያሜ ኢህአዴግ ውህድ ፓርቲ ሊሆን ነው"--- አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@ethio27
14ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በኦሮሚያ ክልል አዘጋጅነት በአዲስ አበባ እንደሚከበር ተገለፀ‼️

14ኛውን የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓልን ለውጡን ተከትሎ ያጋጠሙ ሃገራዊ ችግሮችን ለመቅረፍ በሚያስችል መልኩ ለማክበር ዝግጅት በመደረግ ላይ መሆኑ ተገለፀ።

በዓሉ አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ በድምቀት ይከበራል ያለው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ቅድመ ዝግጀቱን በማስመልከት ከ9ኙ ክልልና ከ2ቱ ከተማ መስተዳድር ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎች እና የፌዴራል ተቋማት ተወካዮች ጋር በመምከር ላይ ነው።

በዓሉ ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ እየተከበረ እንደሚገኝ ያስታወቁት የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ዘንድሮም ለ14ኛ ጊዜ በኦሮሚያ ክልል አዘጋጅነት በአዲስ አበባ እንደሚከበር ተናግረዋል።

ህገ መንግሥቱ በፀደቀ በ25ኛ ዓመት የሚከበር መሆኑ በዓሉን ልዩ ያደርገዋል ያሉት ወ/ሮ ኬሪያ የብሄር ጥላቻንና መካረርን በማስቀረት ህገ መንግሥቱን ባከበረ መልኩ እንዲከበር ጥሪ አቅርበዋል።

አፈ ጉባዔዋ አያይዘውም በአመለካከት ልዩነቶች ሳቢያ በሚፈጠሩ ችግሮች ህዝብ ሰለባ እየሆነ ነው ያሉ ሲሆን በዓሉ ይህንንና መሰል ችግሮችን ለማስቀረት በሚያስችል መልኩ እንደሚከበር ነው ያስታወቁት።
#join በማረግ ለ ጓዋደኞት ያካፍሉ
@ethio27
Forwarded from Safaricom Ethiopia (Love)
እስከ አሁን የዩኒቨርስቲ መግቢያቸውን ያሳወቁ ዩኒቨርሲቲዎች‼️

1.#Addis Ababa university
ነባር ተማሪዎች :-
መስከረም 5-6
አድስ ገቢ ተማሪዎች
አላሳወቀም
2.#mekelle university
ነባር ተማሪዎች :-
መስከረም 5-7
አድስ ገቢ ተማሪዎች
አላሳወቀም
3.#Jimma university
ነባር ተማሪዎች :-
መስከረም 19-20
አድስ ገቢ ተማሪዎች
መስከረም 26-27
4.#Arbaminch university
ነባር ተማሪዎች :-
መስከረም 21-22
አድስ ገቢ ተማሪዎች
መስከረም 28-29

5.#Gonder university
ነባር ተማሪዎች :-
መስከረም 22-23
አድስ ገቢ ተማሪዎች
መስከረም 28-29

6.#Wollagga university
ነባር ተማሪዎች :-
መስከረም 19-20
አድስ ገቢ ተማሪዎች
መስከረም 26-27

7.#Arsi university
የህክምና ስፔሻሊስት
መስከረም 20-21
ነባር ተማሪዎች :-
መስከረም 22-23
አድስ ገቢ ተማሪዎች
አላሳወቀም

8.#Wachamo university
ጤና ተማሪዎች
መስከረም 5-6
ነባር ተማሪዎች :-
መስከረም 21-22
አድስ ገቢ ተማሪዎች
መስከረም 28-29

9.#Assosa university
ነባር ተማሪዎች :-
መስከረም 20-21
አድስ ገቢ ተማሪዎች
አላሳወቀም

10.#Wollo university
ነባር ተማሪዎች :-
መስከረም 24-25
አድስ ገቢ ተማሪዎች
ጥቅምት 1-2

11.#Aksum university
የጤና ተማሪዎች
መስከረም 8-9
ነባር ተማሪዎች :-
መስከረም 19-20
አድስ ገቢ ተማሪዎች
አላሳወቀም

12. #Dilla Univeristy
ነባር ተማሪዎች
መስከረም 21-22
አዲስ ገቢ ተማሪዎች
መስከረም 26-27

13.#Debra_tabor Univeristy
ነባር ተማሪዎች
መስከረም። 19-21
አዲስ ገቢ ተማሪዎች
መስከረም 23-25

14.#Debra_markos Univeristy
ነባር ተማሪዎች
መስከረም 21-22
አዲስ ገቢ ተማሪዎች
መስከረም 28-29

15.#Haramaya Univeristy
ነባር ተማሪዎች
መስከረም 28-30
አዲስ ገቢ ተማሪዎች
ጥቅምት 3-5

16.#Bonga Univeristy
ነባር ተማሪዎች
መስከረም 24-26
አዲስ ገቢ ተማሪዎች
አላሳወቀም
17. #woldiya university
ነባር ተማሪዎች
መስከረም 22-23
አዲስ ገቢ ተማሪዎች
መስከረም 28-29
18.#Debra_birhan Univeristy
ነባር ተማሪዎች
መስከረም 19-20
አዲስ ገቢ ተማሪዎች
መስከረም 26-27
20.#Bahirdar Univeristy
ነባር ተማሪዎች
መስከረም 26-27
አዲስ ገቢ ተማሪዎች
no
(@NEAEA2012 ዘገባ)
21. #Ambo Univeristy
ነባር ተማሪዎች
ጥቅምት 3-4
አዲስ ገቢ ተማሪዎች
No
22.#Worabe Univeristy
ነባር ተማሪዎች
መስከረም 19-21
አዲስ ገቢ ተማሪዎች
መስከረም 26-27

23.#Adigrat Univeristy
ነባር ተማሪዎች
መስከረም 26-27
አዲስ ገቢ ተማሪዎች
No
24. #Wolayta Univeristy
ነባር ተማሪዎች
መስከረም 20-21
አዲስ ገቢ ተማሪዎች
መስከረም 27-28
25.#Dirre_dawaUniveristy
ነባር ተማሪዎች
መስከረም 26-27
አዲስ ገቢ ተማሪዎች
ጥቅምት 3-4

25.#Madda_walabu Univeristy
ነባር ተማሪዎች
መስከረም 26-27
አዲስ ገቢ ተማሪዎች
የለም
26.#Wolkite Univeristy
ነባር ተማሪዎች
መስከረም 26-27
አዲስ ገቢ ተማሪዎች
No

⚠️ሌሎች ዩንቨርስቲዎች አላሳወቁም!
#join በማረግ ለ ጓዋደኞት ያካፍሉ
@ethio_fik @ethio_fik @ethio_fik @ethio_fik
የቀድሞው የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን የ80 ቀን መታሰቢያና ሃውልት ምረቃ በመቐለ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስተያን ተፈፅሟል!

Via Petros Ashenafi Kebede
@kushtikbot
ትኩረት ለድሬዳዋ!

የእሬቻ የሩጫ ፕሮግራም እና የኦርቶዶክስ ቤ/ክ ሰልፍ በሰላም ተጠናቋል። ድሬዳዋ ግን ረብሻ ተከስቶ ሰዎች ጭንቅ ላይ እንዳሉ መልእክት እየደረሰኝ ነው። እባካችሁ የሚመለከታችሁ አካላት ትኩረት ስጡልን።

ሰላም ለሀገራችን!
@kushtikbot
⬆️
በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ዝግጅት የነበራቸው 12 የአልሸባብ እና የአይ ኤስ የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ!

የብሄራዊ የመረጃ ደህንነት አገልግሎት ይህንኑ ለኢቢሲ የላከው መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል:

አልሸባብ እና አይ ኤስ የሽብር ቡድኖቻቸውን ወደ አዲስ አበባ እና የተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች በመላክ በኢትዮጵያ የሽብር ጥቃት በመፈፀም በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳይ ለማድረስ እንዲሁም የሀገራችንን በጎ ገፅታ ለማበላሸት በዝግጅት ላይ እንዳሉ ብሄራዊ የመረጃ ደህንነት አገልግሎት ባደረገው ጥብቅና የተቀናጀ ክትትል ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን በቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርጓል፡፡

ይሄንን የጥፋት ተግባር ለመፈፀም ሀገር ውስጥ የገባው አንድኛው የአልሸባብ የሽብር ቡድን በሙሐመድ አብዱላሂ ዱለት በሀሰተኛ ስሙ ያህያ አሊ ሃሰን የሚመራ ሲሆን የሽብር ጥቃት ተልዕኮ ይዞ በጅቡቲ በኩል ወደ አዲስ አበባ ከተማ በመግባት ህዝብ የሚባዛባቸውን ቦታዎች እንዲሁም የሀይማኖት ክብረ በዓል የሚካሄድባቸውንና የተለያዩ ሆቴሎችን የመለየትና የፎቶግራፍ መረጃዎችን የመሰብሰብ ጥናት ካደረገ በኃላ ወደ ሽበር ተግባራ ለመግባት በዝግጅት ላይ እንዳለ በብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ከጅቡቲ ወደ ሀገራችን ሲገባ ጀምሮ ክትትል ሲደረግበት ስለነበር በአዲስ አበባ ቦሌ አካባቢ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

ከእርሱ ጋር በመሆን የተለያዩ ጥናቶችን ሲያካሄዱ የነበሩና ጁቡቲ የሚገኙ አብደክ መሃመድ ሁሴንና ሬድዋን መሃመድ ሁሴን የተባሉት ግብረአበሮቹም ጅቡቲ ከሚገኘውና ሁኔታውን ሲያመቻችላቸው ከነበረው ሌላ የአልሸባብ አባል በቅፅል ስሙ ስመተር መሀመድ ኢማን ዩሱፍ የተባለውን ጨምሮ ከሀገሪቱ የመረጃ ተቋም ጋር በመቀናጀት በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል፡፡

አልሸባብ የሽብር ጥቃት እንዲፈፅሙ ካሰማራቸው ሌሎች ቡድኖች ውስጥም ከደቡባዊ ሶማሊያ ተነስተው ሱማሊላንድ ሐርጌሳ ከተማ ከገቡ በኋላ ወደ ሀገር ውስጥ ለመግባት ዝግጅት ሲያደርጉ ከነበሩ ሌሎች የሽብር ቡድኑ አባላት መካከልም ይሳቅ አሊ አደንና አደን ሙሃሙድ መሃመድ በቅፅል ስሙ አደን ቦራይ የተባሉት የፈንጅና የአጥፍቶ መጥፋት ስልጠና የወሰዱና የቡድኑ ቁልፍ አባላት ከመነሻቸው ጀምሮ በተደረገባቸው ክትትል ከሱማሊላንድ የመረጃ ተቋም ጋር በመቀናጀት በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ሶማሊላንድ በቁጥጥር ስር ከዋሉት ሌሎች የአልሸባብ ሽብር ቡድን አባላት መካከል ኢሳቅ አሊ አደን የተባለው የሽብር እቅዱን ለመፈፀም እንዲያመቸው ከሶማሊያ ክልል ቦህ ወረዳ ጨርቃን ቀበሌ ኢብራሂም ዓሊ አደን በሚል ሃሰተኛ የነዋሪነት መታወቂያ በእጁ ይዞ የተገኘ ሲሆን አደን ማሕሙድ መሐመድ ወይም አደን ቦራይ የተባለው በበኩሉ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁለት የሂሳብ አካውንት በመክፈት ለሽበር ተልዕኮ መፈፀሚያ ሊጠቀሙበት የነበረ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ በተደረገው ጥብቅ ክትትል መገኘቱን ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

ከእነዚህ በተጨማሪም ተመሳሳይ ተልእኮ ይዞው ወደ ሃገር ውስጥ ከገቡት መካከል ዒድ መሃመድ ዓሊ የተባለው በሶማሊ ክልል ጨርጨር ዞን አራርሶ ወረዳ፣ በሽር ዑስማን አብዲ በዚሁ ክልል ፊቅ አከባቢ እንዲሁም ዑስማን አሊ ሁሴን የተባለው በኦሮሚያ ክልል በሞያሌ ከተማ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

በተያያዘ በኢትዮጵያ ላይ በተደጋጋሚ የሽብር ጥቃት እንደሚፈጽም ሲዝት የነበረው ሁለተኛው የአይ ኤስ የሽብር ቡድን ደግሞ ከቦሳሶ በሶማሌላንድ ሃርጌሳ በኩል ወደ አዲስ አበባ በመግባት የሽብር ጥቃት ለመፈፀም ሲንቀሳቀስ በብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት በተደረገበት ጥብቅ ክትትል ፋዕድ አብሽር የሱፍ የተባለው የቡድኑ አባል አዲስ አበባ ቦሌ አካባቢ በቁጥጥር ስር እንዲውል የተደረገ ሲሆን ፤ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የዚሁ ቡድን አባላት መካከልም ሙህመድ ጉሀድ ቡዲል የተባለው በሱማሌ ክልል በአፍዴር ዞን ምዕራብ ኢሚ ወረዳ በቁጥጥር ስር ዉሏል፡፡ ሌላ በሀገር ውስጥ የአይ ኤስ የሽብር ቡድን አባል የሆነ ሰይድ ዑመር ሸበሺ የተባለው በፀጥታ አካላት በአዋሽ አካባቢ በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጓል፡፡

እነዚህ አሸባሪዎች የጥፋት ተለዕኮቸውን ለማስፈፀም የሚጠቀሙባቸው የግንኙነት መሳሪያዎችና ሌሎች ቁሳቁሶች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል፡፡ የሸብር ቡድኖችን በመከታተል በቁጥጥር ሰር እንዲውሉ ለማድረግ በተካሄደው ሰፊ የኦፕሬሽን ስራም የተለያዩ የፌዴራልና የክልል የፀጥታ አካላት እንዲሁም የተለያዩ ሃገራት አጋር የመረጃ ተቋማት ድጋፍ አድርገዋል፡፡ በተለይም ደግሞ የጁቡቲ፣ የሶማሊላንድ፣ የፑንትላንድ የአሜሪካ፤ የጣሊያን፣ የፈረንሳይና የስፔን የመረጃ ተቋማት እገዛ ማድረጋቸውን ብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት በመግለጫው አሳውቋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አግልግሎት በከፍተኛ ክትትል ያገኛቸውን መረጃዎች ለአሜሪካ፣ ለአውሮፓ፤ ለመካከለኛው ምስራቅ እንዲሁም ለአፍሪካና ለኤዢያ በአጠቃላይ 16 ለሚሆኑ ሀገራት ከተያዙት የሽብር ቡድኖች ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የተደረሰባቸውን የሽብር ቡድኑ ህዋስ አባላት በሀገራቱ እንደሚገኙ የሚያረጋግጥ የመረጃ ልውውጥ በማድረግ የበኩሉን ድርሻ ተወጥቷል፡፡

አሸባሪዎቹ በሀገራችን ህዝብ በሚበዛባቸው ቦታዎች፤ ሆቴሎች፤ በመንግስትና በግል ተቋማት እንዲሁም የሃይማኖት ክብረ ባዓላት በሚከበርባቸው ስፍራዎች በፈንጂ ፍንዳታና በተኩስ የታጀበ የሸብር ጥቃታ በመፈፀም በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት ለማድረስ ተዘጋጅተውበት የነበረው የሽብር ጥቃትም የከሸፈው በህብረተሰቡ ከፍተኛ ተሳትፎ መሆኑን ብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት መግለፅ ይወዳል፡፡

በቀጣይም የሽበር ቡድኑ በሀገራችን ጥቃት ለመፈፀም ካለው ዝግጅት አንጻር ህዝባችን ይሄን ተገንዝቦ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደረግና የተለየ ነገር ሲመለከትም በአካባቢው ላለ የፀጥታ አካል መረጃ በመስጠት የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመግለፅ፤ ብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አግልግሎት በሀገራችንና በህዝባችን ብሄራዊ ጥቅምና ደህንነት ላይ የሚቃጡ ማናቸውንም የሽብር ጥቃቶች አስቀድሞ በማወቅ ሙያዊ ብቃቱን በማሳደግ ላይ ያለ ተቋም መሆኑን በመገንዘብ የመላው ህዝባችን ድጋፍ እንዳይለየው አብክሮ ጥሪ ያቀርባል፡፡ @kushtikbot
ጎንደር አካባቢ ተከስቶ የነበረው ችግር የተቀነባበረ ሴራ መሆኑን የፖለቲካ ፓርቲዎችና ድርጅቶች ተናገሩ❗️

ሰሞኑን በማዕከላዊ ጎንደር ዞንና በጎንደር ከተማ የተከሰተው የፀጥታ ችግር የክልሉን ሠላም በማይፈልጉ ኃይሎች የተቀናበረ ሴራ መሆኑን በጎንደር የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ድርጅቶች ገለጹ፡፡

ሐሳባቸውን ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት የሰጡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ‹‹ችግሩ ሆን ተብሎ የክልሉን ሠላም ለማደፍረስ በሦስተኛ ወገን የተጠነሰሰ ሴራ ነው›› ብለዋል።

ከፖርቲዎች መካከል የአማራ ብሔር ንቅናቄ (አብን) የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አስተባባሪ አቶ ደሞዝ ካሴ በደረሰው የሕይወት መጥፋት፣ የአካል መጉደልና የንብረት መውደም የተሰማቸውን ሐዘን ገልፀው ‹‹የአማራና የቅማንት ሕዝብ ለዘመናት አብረው የኖሩ ናቸው። ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአማራን ሕዝብ አንድነት በማይፈልጉ ኃይሎች በተቀነባበረ ሁኔታ አሳፋሪ ግጭት እንዲከሰት ሆኗል፤ ይህም ለረጅም ዘመናት ሲሰራ የኖረ የሴራ ውጤት ነው›› ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሥራ አስፈፃሚ አርበኛ መዓዛው ጌጡ ደግሞ ትርምሱ በሦስተኛ ወገን ተንኳሽነት የመጣ መሆኑን ጠቅሰው ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ችግር በመተማና አካባቢው ሲፈጠር ምንም ዓይነት እርምጃ ባለመወሰዱ አሁንም ቀውሱ እንዲፈጠር ምክንያት መሆኑን አብራርተዋል።

የጎንደር ከተማ አስተዳድር አዴፓ ጽሕፈት ቤት ተወካይ አቶ መስፍን ዓለምነው ደግሞ ተልዕኮ የተሰጣቸው ጽንፈኛ ኮሚቴዎች ምንም ዓይነት ልዩነት የሌለውን ሕዝብ ለመነጠል የሚያደርጉት እንቅስቀሴ መሆኑን ጠቅሰው ‹‹ሦስተኛ ወገን የሚባለው የሚሸፋፈን ሳይሆን ትህነግ (ህወኃት) ነው›› ብለዋል። አዴፓ ከወጣቶች ጋር በመቀናጀት የተሻለ ሠላም እንዲመጣ እየሠራ መሆኑንም ተናግረዋል።

‹‹ችግሩ በአጭር መቆም እየቻለ እዚህ ደረጃ መድረስ አልነበረበትም›› ያሉት አርበኛ መዓዛው ‹‹አሁንም አዴፓ ከሕዝቡ ጋር ተቀራርቦ መሥራትና አጥፊዎችን ለሕግ ማቅረብ ይጠበቅበታል›› ብለዋል። አያይዘውም ወጣቱ ከስሜት ነፃ ሁኖ አካባቢውን እንዲጠብቅና የሴረኞች ዓላማ አስፈፃሚ እንዳይሆን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚኖርበት አሳስበዋል።

©አብመድ

@ethio27 @ethio27
@ethio27 @ethio27
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ነገ ይጀምራል❗️

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሥራ ዘመን በሕገ መንግሥቱ በተደነገገው መሠረት በመስከረም ወር የመጨረሻው ሰኞ ሥራ ይጀምራል፡፡ በዚህም መሠረት ነገ መስከረም 26 ቀን 2012ዓ.ም የ5ኛ ዙር 5ኛ ዓመት ሥራውን በይፋ ይጀምራል፡፡

የመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላትና አፈ ጉባኤዎች በተገኙበት በኢፌዴሪ ፕረዚዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ ንግግር እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች፣ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች፣ የሃይማኖት አባቶች እና ታዋቂ ግለሰቦችም በመክፈቻ መርሀ ግብሩ እንደሚገኙ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቋል፡፡

©አብመድ

አሥተያየቶችን እዲሁም መረጃወችን በዚህ አድርሡኝ ፡- @Lion7682

@ethio27 @ethio27
በአጣዬ 8 ሰዎች ተገደሉ ተባለ።

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ ከተማና አካባቢዉ ከትናንት በስቲያ በተቀሰቀሰዉ ግጭት የ5 ሰላማዊ ዜጎች እና ሕይወት ማለፉ ተገለፀ። በግጭቱ ከመንግሥት ወገን 3 የፀጥታ ኃይላት መሞታቸውንና 5 መቁሰላቸውም ተገልጧል።

የአጣዬ ከተማ ከንቲባ አቶ ጌታቸዉ በቀለ እንደገለፁት በአካባቢዉ ግጭቱ የተቀሰቀሰዉ ከ3 ቀን በፊት አንድ የታጠቀ ግለሰብ የክልሉ ልዩ ኃይል በሚገኝበት የጥበቃ ማማ ላይ በከፈተዉ ተኩስ ነዉ።

ግለሰቡ ጦር መሣሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በማይቻልበትና በኮማንድ ፖስት ስር ባለ አካባቢ 3 የእጅ ቦንቦች፤ ክላሽንኮቭ እና በርካታ ጥይቶችን ይዞ በመገኘቱ በተኩስ ልዉዉጥ እንደተገደለ አቶ ጌታቸዉ ዐስታዉቀዋል።

ይህንን ተከትሎ ያለፉት 3 ቀናት በአጣዬ ከተማና በአካባቢዉ በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች ጭምር በርካታ ቁጥር ያላቸዉና «ያልታወቁ »ያሏቸዉ የታጠቁ ኃይሎች በአካባቢዉ ነዋሪዎች ላይ ተኩስ መክፈታቸዉን ተናግረዋል። በዚህ ግጭትም በአካባቢዉ ገጠር ቀበሌዎች የአምስት ሰላማዊ ዜጎች ሕይወት መቀጠፉን ከንቲባዉ አብራርተዋል።

የሰሜን ሸዋ ዞን የመንግስት የኮሚንኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ማሙሽ ይልማ በኩላቸዉ፦ ጥቃቱን ያደረሱት የኦነግ ሰራዊት አባላት መሆናቸዉን ገልፀዉ፤ በግጭቱ ከመንግሥት ወገን 3 መሞታቸውንና 5 መቁሰላቸውን ተናግረዋል፡፡

የኦነግ ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አደባ በስልክ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ «አጣዬ ኦነግ ምን ሊሰራ ይመጣል፣ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሰራዊት እንደሌለው ብዙ ጊዜ መላልሰን ተናግረናል፤ በምንም መልኩ ኦነግ ሰራዊት የለውም።

ሰራዊት የሌለው ድርጅት ደግሞ ለምን ሰሙ እንደሚጠቀስ አናውቅም፡ አጠቃላይ ስሞታው ውሸት ነው። የኦነግን ስም ለማጠልሸት የሚደረግ ነገር ነው” ሲሉ ለባህርዳሩ ዘጋቢያችን ዓለምነዉ መኮነን ገልጠዋል።

እንደ አቶ ጌታቸዉ በአጣዬና በአካባቢዉ ገጠር ቀበሌዎች አሁንም ድረስ ዉጥረት በመንገሱና ተኩስ በመቀጠሉ ምንም አይነት እንቅስቃሴ የለም።

በአካባቢዉ ዉጥረቱን ለማርገብ የክልሉ ልዩ ኃይል፣ የፌደራል ፖሊስና የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሰፍሮ የሚገኝ ሲሆን፤ ተጨማሪ ኃይል እንዲገባ እየተጠየቀ መሆኑንም ከንቲባዉ አመልክተዋል።

ይህን መሰሉ ጥቃት ከዚህ ቀደም በሰኔ ወር 2010 ዓ.ም እና በመጋቢት ወር 2011 ዓ.ም ተቀስቅሶ የሰዉ ሕይወት መጥፋቱን፤ በርካታ ንብረት መዉደሙን እንዲሁም ቤተ እመነቶች እና የመንግስት ተቋማትም መቃጠላቸዉን ኃላፊዉ ለዶይቸ ቬለ አክለው ተናግረዋል።
@ethio27
ዘገባው የዶቸቪሌ ነው
በአዲስ አበባ ከስምንት ዓመት በፊት ተቋርጦ የነበረው የፍትህ አካላት ስልጠና ሊጀመር ነው፡፡

የመጀመሪያ ድግሪ የህግ ተመራቂዎች በየዓመቱ በክልሎች የፍትህ አካላት ስልጠና ይሰጣል፡፡

ይህን ስልጠና ያልወሰዱ ተመራቂዎች ደግሞ ዳኛ ወይም አቃቢ ህግ የመሆን እድል ፈጽሞ የላቸውም፡፡

ይሁንና ከ2004 ዓ/ም ጀምሮ በአዲስ አበባና ድሬዳዋ ይህ ስልጠና እንዳይሰጥ ታግዷል፡፡

ተመራቂዎቹ ወደ ክልሎች ሄደው ለመሰልጠንም መታወቂያና ተጨማሪ ማስረጃዎችን እንደሚጠየቁ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የህግ ምሩቃን አስተያየታቸውን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ሰጥተዋል፡፡

በዚህም ምክንያት በመንግስታዊ መስሪያ ቤት ከተቀጠሩ በኋላ ከስራ እንዲሰናበቱ መደረጋቸውን ያነጋገርናቸው የህግ ባለሙያዎች ነግረውናል፡፡

አቤቱታቸውን ይዘው የቀድሞው ፍትህ ሚኒስቴር እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ድረስ ቢሄዱም ሰሚ ማጣታቸውንና ክስ መስርተው ጉዳዩን ፍርድ ቤት ቢያደርሱትም መፍትሄ አለማግኘታቸውን ነው የነገሩን፡፡

ይህ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ከፍትህ ስርአቱ ለማስወጣት ሲባል የተወሰነ ፖለቲካዊ ውሳኔ ነው ሲሉ ሃሳባቸውን ይገልጻሉ፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም የፌዴራል ፍትህና የህግ ምርምርና ስልጠና ማእከልን ስለጉዳዩ ጠይቋል፡፡

የማእከሉ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘካሪያስ ኤርኮላ ከአውሮፓ ህብረት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ለዚሁ አገልግሎት የሚውል ህንጻ ማሰራታቸውንና ህዳር ላይ የአዲስ አበባና ድሬዳዋ መታወቂያ ላላቸው የህግ ተመራቂዎች ስልጠና መስጠት እንደሚጀመር ነግረውናል፡፡

ይሁንና የመግቢያ ፈተናውን ማለፍ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

የስልጠና ይዘቱ ላይም ማሻሻያ እየተደረገ መሆኑን አቶ ኤርኮላ ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡
ይህ ስልጠና ሙያዊ ሳይሆን ለህግ ባለሙያዎች የመንግስትን ርእዮት አለም የሚያጠምቅ ነው በሚል እንደሚተች ይታወቃል፡፡
@ethio27
በትግራይ ምዕራባዊ ዞን የተከናወኑ ሥራዎች ግብርናን ማዘመን እንደሚቻል ማሳያ ናቸው ተባለ❗️

ከፌዴራል እና ትግራይ ክልል የተውጣጡ ከፍተኛ አመራሮች እና የሥራ ሓላፊዎች የተሳተፉት የመስክ ጉብኝት ከመስከረም 19-20 ቀን 2012 ዓ.ም በትግራይ ክልል፣ ምዕራባዊ ዞን፣ የሰቲት እና ቓፍታ ሑመራ አካባቢ ተካሂዷል።

በዚሁ የሰቲት እና ቓፍታ ሑመራ ጉብኝት አርሶ አደሮች ያከናወኑት የሰብል፣ የፍራፍሬ እና የእንስሳት ልማት እንዲሁም በዘመናዊ ግብርና የመጠቀም ፍላጎታቸው እያየለ መምጣት በኢትዮጵያ ግብርናን ማዘመን እንደሚቻል ማሳያ ናቸው፤ ሽግግሩንም ያፋጥናሉ ሲሉ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሳኒ ረዲ ገልጸዋል።

በዞኑ ውስጥ በረከት እና ማይ ካድራ በተባሉ አካባቢዎች በሰሊጥ እርሻ ልማት ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች እና አርሶ አደሮች በበኩላቸው፣ የኤሌክትሪክ ኃይል፣ ማሽነሪ እና ብድር አቅርቦቶች እጥረት ከተቀረፉ ራሳቸውንና አገራቸውን ይበልጥ ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚችሉ ተናግረዋል። አቶ ሳኒም ከባለሀብቶቹ እና አርሶ አደሮቹ ለተነሡ የእገዛ ጥያቄዎች ምላሽ የሚሆኑ የመፍትሔ አማራጮችን ጠቁመዋል።

በእጅ ካሉ አማራጮች በተጨማሪ ወጣቶችን በማሽነሪ ኪራይ አገልግሎት የማደራጀት እንዲሁም የግብርና ማይክሮ ፋይናንስ እና የግብርና ኢንሹራንስ አሠራሮችን የማጸደቅ እና የማስፈን ሥራዎች መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ የሚሠራቸው ዐበይት የቤት ሥራዎች እንደሚሆኑ አቶ ሳኒ ማስረዳታቸውን ከግብርና ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ አመልክቷል።

©EBC

@ethio27 @ethio27
ብርሃንና ሰላም በውጭ ምንዛሬ ችግር የህትመት ሥራዎችን ሊያቆም እንደሚችል አስታወቀ!

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት የውጭ ምንዛሬ በአስቸኳይ ካልለቀቀለት ጋዜጦችን፣ፈተናዎችንና ሌሎች ህትመቶችን ከሁለት ወራት በኋላ ማተም ሊያቆም እንደሚችል ገለጸ።

የድርጅቱ የኮርፖሬት ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጌታሁን ነጋሽ ‹‹ለህትመት መሰረታዊ የሆኑት ወረቀት፣ ቀለም፣ ፕሌት፣ ኬሚካልና ሌሎች 90 በመቶ የሚሆኑት ግብዓቶች ከውጭ አገር ስለሚገቡ የውጭ ምንዛሬ ያስፈልጋል።

ከግብዓት በተጨማሪም መለዋ ወጫና አዳዲስ ማሽኖችን ለመግዣ የውጭ ምንዛሬ ያስፈልጋል። ለድርጅቱ ከአንድ ዓመት በላይ የውጭ ምንዛሬ እንዲፈቀድልን ጥያቄ ብናቀርብም እስከዛሬዋ ዕለት ድረስ አልተፈቀደልንም።

በተለይም ባለፉት ስድስት ወራት ለብሄራዊ
ባንክ ሊያጋጥመን የሚችለውን ችግር በስፋት አስረድተናል፤ ነገር ግን መፍትሄ አልተሰጠንም›› ብለዋል።

Via ኢ.ፕ.ድ
በጭልጋ ወረዳ 45 የአማራ ልዩ ኃይል ሕይወት አለፈ!!

በማዕከላዊ ጎንደር ጭልጋ ወረዳ ከአይከል ከተማ፣ ጓንግ እና ቡሆና ድረስ ከመስከረም 17/2012 ጀምሮ ለአምስት ቀናት የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ በአካባቢው የነበሩ ታጣቂዎች በከፈቱት ድንገተኛ ተኩስ ሰላም በማስከበር ላይ የሚገኙ 45 የአማራ ክልል የልዩ ኃይል አባላትን መግደላቸውን የአዲስ ማለዳ ምንጮች አረጋገጡ።

ማክሰኞ መስከረም 20/2012 በባህርዳር በሚገኘው ጽሕፈት ቤታቸው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የተናገሩት የአማራ ክልል የሰላምና ሕዝብ ደኅንነት ቢሮ ኃላፊ አገኘሁ ተሻገር፣ የፀጥታ አካላት ወደ ማደሪያ ካምፓቸው ሲገቡ ከበባ እንደተፈፀመባቸው እና ‹‹ከደረሰባቸው ውርጅብኝ›› ራሳቸውን መከላከላቸውን ይናገራሉ።

@ethio27
#update | ወሎ ዩኒቨርስቲ የአዲስ ተማሪዎች መግቢያ ጥቅምት 4 እና 5 ሆኗል፡፡

አሥተያየቶችን እዲሁም መረጃወችን በዚህ አድርሡኝ ፡@Lion7682

@ethio27 @ethio27
2024/04/30 07:32:58
Back to Top
HTML Embed Code: